ቀን፡- መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ዓባይ ባንክ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የሥራ ቦታ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
- የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የጥበቃ ሠራተኛ
- የሥራ ቦታ፡- አዲስ አበባ ዋናው መሥሪያ ቤት ሆኖ በተደጋጋሚ የመስክ ሥራ ያለው
- የቅጥር ሁኔታ፡- በቋሚነት
- ጾታ፡- ወንድ
- የትምህርት ዝግጅት፡- በቀድሞው 12ኛ ክፍል ወይም በአዲሱ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ
- ዕድሜ ፡- ከ40 ዓመት ያልበለጠ
- ተፈላጊ የሥራ ልምድ፡- በመከላከያ ወይም በፖሊስ ሠራዊት ውስጥ ቢያንስ 4 ዓመታት ያገለገለ እና ከተቋማቱ የለቀቀበት ህጋዊ የአገልግሎት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት፣ መልካም ስነ-ምግባር ያለው፣ የተሟላ የአካላዊ ብቃትና ጤናማ የሆነ፣ የፖሊስ ወይም የመከላከያ ስልጠና የወሰደ፣ በቂ የሆነ የጦር መሳሪያ አጠቃቀምና አያያዝ ዕወቀት ያለው፣ ከፖሊስ ወይም ከመከላከያ በዲስፕሊን ችግር ያልተሰናበተ እና ከማንኛውም ሱስ ነጻ የሆነ፣
- መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ዋናውንና ፎቶኮፒ የትምህርት እና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ባምቢስ አካባቢ፣ ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ባለው የሰው ሀብት አስተዳደር መምሪያ በመምጣት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-5549731 ይደውሉ፡፡