ይጠንቀቁ!የፋይናንስ እንቅስቃሴ ደህንነትዎን ይጠብቁ! Solomon Aynishet September 1, 2026

ይጠንቀቁ!የፋይናንስ እንቅስቃሴ ደህንነትዎን ይጠብቁ!

photo 2026 08 31 20 47 44

በአንዳንድ አጭበርባሪዎች ሊከሰት ከሚችል የማታለል ተግባር ለመጠበቅ የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ እንድታደርጉ እናሳስባለን፦

🫆 የእርስዎን የባንክ መረጃዎች ማለትም የምስጢር ቁጥሮች (PIN Code)፣ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) ወይም ሌሎች የይለፍ ቃሎችን (Passwords) ለማንም አይስጡ። ዘወትር ከሞባይል መተግበሪያው በአግባቡ መውጣትዎን (Log-out) ማድረግዎን አይዘንጉ።

📥 ስልክዎ ባንክዎ ነውና፣ በነጣቂዎች እንዳይወሰድ ይጠንቀቁ፤ በማናቸውም የማኅበራዊ ሚዲያ ትሥሥር ገጾች አማካኝነት የሚደርስዎን አጠራጣሪ ማገናኛ (Links) አይክፈቱ፤ ለማያውቁት መልዕክትም ምላሽ አይስጡ።

📞 ማንኛውም የማጭበርበር ሙከራ ካጋጠምዎ፣ ስልክዎ ከጠፋ ወይም ከተሰረቀ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ያነጋግሩ ወይም ወደ ደንበኞች የጥሪ ማዕከል 8834 ይደውሉ፡፡

🛒 ግብይትዎን በዓባይ ሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ያድርጉ። መተግበሪያውን ከ 👉 https://www.abaybanksc.com/mobile_app ያውርዱና ስልክዎ ላይ ይጫኑ ወይም በUSSD በ*812# ላይ በመደወል የባንክ አገልግሎት ያግኙ!

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!