የጥንቃቄ መልዕክት (Fraud Alert!) Solomon Aynishet May 21, 2026

የጥንቃቄ መልዕክት (Fraud Alert!)

photo 2026 05 21 09 34 40

ውድ ደንበኛችን፣

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ሒሳብ ቁጥርን ከፋይዳ  መለያ  (Fayda ID)  ጋር ለማስተሳሰር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ መጠናቀቅ ተከትሎ፣ ከባንክ የተደወለ በማስመሰል የሚደረጉ የማጭበርበር ሙከራዎች መኖራቸውን ተረድተናል።

በመሆኑም ራስዎን ከዚህ አይነት አጭበርባሪዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ እናሳስብዎታለን።

●  የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን፣ የባንክ መረጃዎችዎን፣ PIN ወይም ፓስዎርድዎን ለማንም አይስጡ፣

●  የፋይዳ መለያን ከባንክ ሒሳብ ጋር በበይነ-መረብ (Internet) ለማስተሳሰር  ይህን ማገናኛ  (ሊንክ)  https://faydaabaybank.com.et/ በመጠቀም ወይም ወደሚቀርብዎ የባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ብቻ ያስተሳስሩ፣

●  በበይነ-መረብ ለማስተሳሰር እርዳታ ሲያስፈልግዎ ከማያውቁትና ከማያምኑት ሰው እገዛ በፍጹም አይጠይቁ፣

●  ባንካችን የፋይዳ መለያ ወይም የባንክ መረጃዎችን በስልክ ወይም በጽሑፍ መልዕክት እንደማይጠይቅ ተረድተው፣ የባንክ ሠራተኞች ነን' ወይም የፋይዳ ባለሙያዎች ነን’ ብለው ለሚደውሉ አጭበርባሪዎች መረጃ ከመስጠት ይቆጠቡ፣

●  ከተጠቀሰው የባንካችን የፋይዳ ቁጥር ማስተሳሰሪያ ማገናኛ (ሊንክ) ውጭ ተመሳስሎ የተሰራ፣ እንዲሁም ማንኛውንም ማገናኛ  አይጫኑ፤ መሰል ያልታወቁ መልዕክቶችንም አይክፈቱ።

የሚያጠራጥሩ ጉዳዮች ካጋጠሙዎ፣  ወደ ነጻ የጥሪ ማዕከላችን 8834 በመደወል ያሳውቁን።

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!