የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የባንኩን የ15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክተው በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምላኩ አስረስ (ዶ/ር) በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው ባንኩ የ15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር በበርካታ ስኬቶች በታጀበ ውጤት ጋር በመሆኑ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
ለባንኩ የሥራ አመራሮች፣ ሰራተኞች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ባንኩ እያስመዘገበ ያለውን ሁለንተናዊ ስኬት በማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ከዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበውን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በመቀበል ቦርዱ ላቀረበው መልካም ምኞትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ዓባይ ባንክ 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ከሐምሌ 7/2017 ጀምሮ በተለያዩ መርሃግብሮች በድምቀት በማክበር ላይ ይገኛል፡፡