የዓባይ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በቅርቡ የተገነባውን እና ሸጎሌ አካባቢ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን(ኢቢሲ) የሚዲያ ኮምፕሌክስ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም ወቅት የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ለዓባይ ባንክ የሥራ ኃላፊዎች የሚዲያ ኮምፕሌክሱን አስመልክተው ሰፊ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፣ ተያይዞም ከዓባይ ባንክ ጋር ባላቸው የሥራ አጋርነት ባንኩ እየሰጠ ያለውን ቀልጣፋ አገልግሎት አድንቀው በቀጣይም ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡
የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በበኩላቸው ባንኩ የኢቢሲ የሥራ አጋር መሆኑን እና በርካታ የባንክ አገልግሎቶችን እያቀረበ መሆኑን አስታውሰው፣ በቀጣይም ከኢቢሲ ጋር ለውን የሥራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ፣ የስትራቴጂ ዋና መኮንን አቶ ወንድይፍራው ታደሰ እና የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሰፋ ተፈራ በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡