የዓባይ ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባኤዎች የጥሪ ማስታወቂያ
የማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ ብር 7,089,001,000.00
የምዝገባ ቁጥር MT/AA/20031268/2007
ዋና መሥሪያ ቤት፣ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 8፣ የቤት ቁጥር አዲስ
የዓባይ ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባኤዎች ሕዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ኢንተር ሌግዤሪ አዲስ ሆቴል ስለሚካሄዱ የባንኩ ባለአክስዮኖች በተጠቀሰው ቀን ሰዓት እና ቦታ በስብሰባው እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. የ16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
1.1. ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣
1.2. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
1.3. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
1.4. የአዳዲስ አክሲዮኖች ሽያጭ እና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፣
1.5. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፣
1.6. የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፣
1.7. የዘመኑ የተጣራ ትርፍ አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
1.8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አበልና የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
1.9. የውጭ ኦዲተር ሹመት ማጽደቅና ክፍያ መወሰን፣
1.10. የቦርድ አባላት ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ ወይም መሰየም፣
1.11. የቦርድ አባላት ምርጫ ማካሄድ፣
1.12. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣
2. የ8ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
2.1. ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣
2.2. ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
2.3. የጉባኤውን ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣
2.4. የባንኩን መመሥረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣
2.5. የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ፣
ማሳሰቢያ
ባለአክስዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ቅጅውን በመያዝ በግንባር በመገኘት ወይም የባለአክስዮኖች ህጋዊ ተወካዮች አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሠጠ ውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የወካይና ተወካይ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዛችሁ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክስዮኖች ከስብሰባው ዕለት ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ባንኩ ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
በተጨማሪም ጆሞ ኬንያታ መንገድ፣ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንጻ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0115571228 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዓባይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ