​የዓባይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 9ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ የጥሪ ማስታወቂያ Solomon Aynishet October 30, 2026

​የዓባይ ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 9ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ የጥሪ ማስታወቂያ

photo 2026 05 28 17 18 42 1

​​የዓባይ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 9ኛ አስቸኳይ ድንገተኛ ጉባዔ ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ የስብሰባ አዳራሽ ይካሄዳል። ​

ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል። ​

  1. የ17ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡- ​

1.1 ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣

1.2 ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ፣

1.3 የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣

1.4 የአዳዲስ አክሲዮኖች ሽያጭ እና የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፣

1.5 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፣

1.6 የውጭ ኦዲተሮች ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ መወሰን፣

1.7 የዘመኑ የተጣራ ትርፍ ክፍፍል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

1.8 የዳይሬክተሮች ቦርድ አበልና የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣

1.9 የውጭ ኦዲተር ሹመት ማጽደቅና ክፍያ መወሰን፣

1.10 የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ​

2. የ9ኛው አስቸኳይ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡- ​

2.1 ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ማጽደቅ፣

2.2 ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣

2.3 የጉባዔውን ረቂቅ አጀንዳ ማጽደቅ፣

2.4 የቦነስ አክሲዮኖች (Bonus shares) ላይ ተወያይቶ መወሰን፣

2.5 የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ ተወያይቶ መወሰን፣

2.6 የባንኩን መመስረቻ ጽሑፍ ማሻሻል፣

2.7 የጉባዔውን ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ:- ​

በጉባዔው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከስብሰባው ዕለት ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ባንኩ ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። ​

በተጨማሪም ጆሞ ኬንያታ መንገድ፣ ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንፃ በሚገኘው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-557-12-28 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

የጠቅላላ ጉባኤውን አጀንዳዎች እሑድ ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ.ም በወጣው የሪፖርተር አማርኛ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ መመልከት ይችላሉ፡፡

የዓባይ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ