የአገልግሎት አሰጣጥ እና የደንበኞቻችን ምስክርነት Solomon Aynishet May 23, 2026

የአገልግሎት አሰጣጥ እና የደንበኞቻችን ምስክርነት

3H0B9656

ባንካችን በሚሠጠው የተሻለ አገልግሎት ደንበኝነታቸው ለረዥም ዓመት እንዲዘልቅ ምክንያት መሆኑን የመሀል ወሰን አካባቢ ቅርንጫፍ ደንበኞች ተናገሩ።

ባንካችን እያካሄደና ባለው ዓባይ ሰዲቅ ከወለድ ነጻ ልዩ የደንበኞች ወር አገልግሎት እየሰጡ ካሉ ቅርንጫፎቻችን አንዱ የሆነው የመሀል ወሰን አካባቢ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍስሐ አይችሉህም እንደገለጹት፣ ዓባይ ባንክ ባዘጋጀው የዓባይ ሰዲቅ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ልዩ የደንበኞች ወር በርካቶች ወደ ቅርንጫፉ በመምጣት እየተገለገሉ ነው።

በመሀል ወሰን ቅርንጫፉችን ደንበኛ የሆኑት አቶ ወልደጋብር ቁርባን ባንካችን እየሰጠ ባለው ቀልጣፋና ምቹ አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው፣ ለሠራተኞቹም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወጣት አቤል ዘውዴ በበኩሉ ከባንካችን ጋር ከአሥር ዓመት በላይ በደንበኝነት መቆየቱን ገልጾ፣ ለታማኝ ደንበኝነቱ ምክንያት የሆነው ዓባይ ባንክ ደንበኛ ተኮር ፍልስፍና ያለው በመሆኑ ነው ብሎናል። ዓባይ ባንክ በቀጣይም የንግድ ሥራ እንቅስቃሴውን በፋይናንስ ድጋፍ ውጤታማ እንደሚያደርገው እምነቱን ገልጿል፡፡

ግንቦት 1/2018 ዓ.ም. በድምቀት የተጀመረው የዓባይ ሰዲቅ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ልዩ የደንበኞች ወር በሁሉም ቅርንጫፎች እና ለዚህ አገልግሎት ተብለው በተከፈቱ ቅርንጫፎቻችን ምቹ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ወደቅርንጫፍ መምጣት ካልቻሉ፣ በደጂታል የባንክ አገልግሎት መስጫ አማራጮች ማለትም በዓባይ የሞባይል መተግበሪያ እና በ *812# USSD ኮድ አገልግሎታችን ተደራሽ ነው።

የሞባይል መተግበሪያውን ከ https://www.abaybanksc.com/mobile-banking-abay ላይ በማውረድ ካሉበት ሆነው ሕይወትዎን ያቅሉ፣ ሥራዎን ያቀላጥፉ።



ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!