የሥነ-ምግባር ጥቆማ (Whistleblowing) – 6969
ዓባይ ባንክ አ.ማ. ከፍተኛ የሥነ-ምግባር፣ የታማኝነት እና የሕግ ተገዢነት መርሆዎችን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ ነው። ባንኩን፣ ደንበኞቹን ወይም ሕዝቡን ሊጎዳ የሚችል ማንኛውንም የሥነ-ምግባር ጥሰት ወይም ሕገ-ወጥ ድርጊት ካዩ ወይም ካወቁ፣ በቅን ልቦና እንዲጠቁሙን ጋብዘንዎታል።
የሚቀርቡ ጥቆማዎች በሚስጥር ይያዛሉ፤ በገለልተኛነት ይመረመራሉ፤ እንዲሁም በቅን ልቦና ጥቆማ የሚያቀርቡ ግለሰቦች በሕግና በባንኩ ፖሊሲዎች መሠረት ይጠበቃሉ።
ሊጠቁሙባቸው የሚችሉ ጉዳዮች፡-
- ማጭበርበር ወይም ስርቆት፣
- ጉቦ ወይም ሙስና፣
- የጥቅም ግጭት፣
- የፋይናንስ ሥነ-ምግባር ጥሰት፣
- ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም፣
- የመረጃ ግላዊነት ወይም የሳይበር ደህንነት ስጋት፣
- ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀት ወይም ሰነድ ማጭበርበር፣
- የባንኩን ፖሊሲዎች ወይም ሕጎችን መጣስ እንዲሁም
- ማንኛውም ሌላ ያልተገባ ድርጊት
ጥቆማዎን በሥነ-ምግባር መከታተያ ክፍል ጥቆማ መስጫ ነፃ የስልክ ቁጥር 6969 ወይም በባንኩ የደንበኞች የጥሪ ማዕከል 8834 በመደወል ያቅርቡ!
የእርስዎ ጥቆማ የባንካችንን ታማኝነት፣ ግልጽነት እና የሥነ-ምግባር ባህል ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
በመተማመን ይጠቁሙ!
ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!