<<የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት እየሠራን ነው>> – አቶ ታደሰ አሰፋ፣ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ፕሬዚዳንት Solomon Aynishet May 29, 2026

<<የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት እየሠራን ነው>> – አቶ ታደሰ አሰፋ፣ የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ፕሬዚዳንት

photo 2026 05 28 20 53 27

የዓባይ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት የአርባምንጭ ቅርንጫፍን አገልግሎት አሰጣጥ ጎበኙ።

በጉብኝቱ የተገኙት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ አሰፋ፣ <<የከተማውን እና በዙሪያው ያለውን ማኅበረሰብ የፋይናንስ ፍላጎት ለማሟላት እየሠራን ነው>> ያሉ ሲሆን፣ የቅርንጫፉ ሠራተኞችን መልካም የሆነ የደንበኞች አገልግሎት ተመልክተው አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠም በጉብኝቱ የተሳተፉ ሲሆን፣ የአርባምንጭ ከተማ ዕድገት ፈጣን በመሆኑ፣ ይህን የኢኮኖሚ ዕድገት እና የነዋሪዎች የዘመነ የባንክ አገልግሎት ፍላጎት ማሟላት ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም በዲጅታል ባንኪንግ ወጣቱን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት መኖሩንም ገልፀዋል።

አቶ የኋላ አያይዘውም ለአንጋፋው የጋሞ ልማት ማኅበር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ግዢ የፋይናንስ አጋር በመሆኑ ዓባይ በቅርበት የሕዝቡ የልማት ደጋፊ እየሆነ ነው ብለዋል።

በአርባምንጭ ከተማ በሁለት ቅርንጫፎች 22,000 ታማኝ ደንበኞች አገልግሎት እያገኙ ሲሆን በዲጅታል የብድር አገልግሎት በርካታ አዳዲስ ደንበኞች ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ ነው።

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!