ዓባይ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ Solomon Aynishet April 17, 2026

ዓባይ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11

ዓባይ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን በአዲስ አበባ ግምገማ አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ፣ የማኔጅመንት አባላት እና የዲስትሪክት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የባንኩ አገልግሎቶች እና አፈፃፀምን በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡

ለሁለት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ በበጀት ዓመቱ የመጨረሻው ሩብ ዓመት ባንኩ ያስቀመጣቸውን ግቦች በስኬት ለማጠናቀቅ በሚቻልባቸው ቁልፍ መንገዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ተደርጓል፡፡