ዓባይ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመትን በስኬት አጠናቀቀ Solomon Aynishet July 20, 2026

ዓባይ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመትን በስኬት አጠናቀቀ

1

ባንካችን ሐምሌ 10 እና 11 ቀን 2018 ዓ.ም የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን፣ በልዩ ልዩ የፋይናንስ እና ፋይናንስ-ነክ ባልሆኑ መለኪያዎች ስኬት በማስመዝገብ ማጠናቀቁን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ የኋላ ገሠሠ አብስረዋል።

የቀጠና ጽ/ቤቶች (ዲስትሪክቶች) እና የተመረጡ ቅርንጫፎች የተሳተፉበት ይህ ጥልቅ ግምገማ፣ የባንኩ ውጤታማነትና የታላቅነት ጉዞ በጠንካራ ሠራተኞቹ የመፈፀም ዐቅም የመጣ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ዓባይ በተከታታይ ዓመታት በስኬት የታጀበ ጉዞው ቀጣይነቱ እንዲረጋገጥ እና በ2026/27 በጀት ዓመትም ግቦቹ እንዲሳኩ አቅጣጫ በመስጠት ለመላው ሠራተኛ አርዓያነት፣ የማኔጅመንት አባላት ትጋት እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በበጀት ዓመቱ የላቀ ስኬት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎችና ቀጠና ጽ/ቤቶች ዕውቅና በመስጠት መርሐ-ግብሩ ተጠናቅቋል።

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!