ዓባይ ባንክ የክፍያ ካርዶች ደህንነት ደረጃ (Payment Card Industry Data Security Standard – PCI DSS) ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመታት የተስማሚነት ምዘና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡
ባንካችን በኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉትን ከፍተኛ የመረጃ ደህንነት መጠበቂያ ደረጃዎችን በማሟላት የውድ ደንበኞቹን የክፍያ ካርድ መረጃዎች ደህንነት በከፍተኛ ጥንቃቄ የተጠበቀ መሆኑን የሚያረጋግጥ በዓለም-አቀፍ ደረጃ የተመሰከረለት ዕውቅና ነው።


ዓባይ ባንክ በቀጣይም ውድ ደንበኞቹ የሚፈጽሟቸውን የክፍያ ልውውጦች ደህንነታቸው በአስተማማኝነት የተጠበቁ እንዲሆኑ የሚያስችሉ አሠራሮችን በማጠናከር በትጋት ይሠራል።
ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!