ዓባይ ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ6ኛ ጊዜ በተዘጋጀው የታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና እና ሽልማት መርሃግብር ላይ ተሸላሚ ሆነ፡፡
የ6ኛው ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ሥነሥርዓት በብሔራዊ ቤተመንግስት ተካሂዷል፡፡
በመርሃግብሩ ላይ 550 ግብር ከፋዮች እውቅና እና ሽልማት ያገኙ ሲሆን፣ ግብር ከፋዮች በሀገር ውስጥ ገቢ በ12 እና በጉምሩክ በ7 የመምረጫ መስፈርቶች መሰረት ተመዝነው እውቅናው ተሰጥቷቸዋል፡፡
የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እውቅና እና ሽልማቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እጅ ተቀብለዋል ፡፡