ዓባይ ባንክ ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራሟል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) ተፈራርመዋል፡፡
ኃላፊዎቹ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ስምምነቱ ልዩ ልዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለሠራተኞች እና እንደተቋም ለኮርፖሬሽኑ በማቅረብ ስትራቴጂያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጡም ባሻገር፣ በፋይናንስ ተደራሽነትና አገራዊ የልማት ሥራዎች ላይ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል።
በስምምነቱ የተካተቱትን የጋራ ግቦች ለማሳካት እና ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሠሩም ኃላፊዎቹ ገልፀዋል።
ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!