ዓባይ ባንክ በድሬዳዋ ዲስትሪክት በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከድሬዳዋና ከአጎራባች አካባቢዎች ከተውጣጡ ባለሃብቶች እና የባንኩ ደንበኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ባንኩ ከዚህ ቀደም ለአሰራር እንቅፋት የነበሩ አካሄዶችን በመቀየር የባንኩ ደንበኞች በተሰማሩበት የተለያዩ የልማት መስኮች እና የስራ ዘርፎች ላይ አስቻይ የሆኑ አሰራሮችን በመዘርጋት ደንበኞቹን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል ። በተጨማሪም ስለባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የተለያዩ አማራጮች እና አሰራሮች ለውይይት ታዳሚዎቹ ሰፊ ማብራሪ እና ገለፃ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የባንኩ ደንበኞች በአሰራርና አፈጻጸም ላይ ሃሳብና አስተያየት የሰነዘሩ ሲሆን በባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል::