ዓባይ ባንክ ከኢትዮጵያ አይ ቲ ፓርክ ጋር በስትራቴጂያዊ የቢዝነስ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሥምምነት በኢትዮጵያ አይ ቲ ፓርክ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈራርመዋል።
የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የኢትዮጵያ አይ ቲ ፓርክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በለጠ እሱባለው የመግባቢያ ሥምምነቱን ተፈራርመዋል፡፡
ኃፊዎቹ ለሁለቱ ተቋሞች ብቻ ሳይሆን ለአገር ዕድገት በሚጠቅሙ ቁልፍ የፋይናንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይም በትብብር እንደሚሰሩ በመርሐ-ግብሩ ተናግረዋል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የማኔጅመንት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!