ዓባይ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር በአጋርነት ለመሥራት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ Solomon Aynishet March 26, 2026

ዓባይ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጋር በአጋርነት ለመሥራት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረመ

photo 2026 03 26 15 23 18

ባንካችን ዓባይ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በስትራቴጂያዊ የቢዝነስ ተግባራት ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ሥምምነት ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራርመዋል።

ተቋማቱን በመወከል የመግባቢያ ሥምምነቱን የፈረሙት የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቤል ታደሠ ለተቋሞቹ እና ለአገር ዕድገት በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ ሁሉ በትብብር እንደሚሰሩ በመርሐ-ግብሩ ላይ አሳውቀዋል።

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!