ዓባይ ባንክ እና በጃይኢትዮ ኢንደስትሪና ኢንጂነሪንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ Solomon Aynishet January 6, 2025

ዓባይ ባንክ እና በጃይኢትዮ ኢንደስትሪና ኢንጂነሪንግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

Agreement

ዓባይ ባንክ አ.ማ.  እና በጃይኢትዮ ኢንደስትሪና ኢንጂነሪንግ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የዓባይ ባንክ የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሰፋ ተፈራ እና የበጃይኢትዮ ኢንደስትሪና ኢንጂነሪንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር በጃይ ናይከር ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ ባንኩ በሚሰጠው የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶች እና በበርካታ የፋይናንስ ዘርፎች በትብብር መስራት የሚያስችል እንደሆነ በፊርማ ሥነ – ሥርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

ዓባይ ባንክ አገልግሎቱን በማስፋፋት ደንበኞቹን የሚመጥኑ የተለያዩ አገልግሎቶች ለመስጠት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም ዘርፈ ብዙ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

Write a comment
Your email address will not be published.