የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ እንደገለፁት ባንኩ በ2026/27 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ችግሮችን በመቋቋም እና ወደ ዕድል በመቀየር የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የቻለበት ነበር ብለዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው አክለውም የተመዘገበውን ውጤት ማዝለቅ እና ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ አሰፋ በበኩላቸው ባንኩ በሩብ ዓመቱ ያስመዘገበው ውጤት የዋና ስራ አስፈፃሚው፣ የማኔጅመንቱ እና የሠራተኞች የተናበበ የስራ ውጤት መሆኑን ገልፀው የተመዘገበውን ውጤት ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ዓባይ ባንክ የ2026/27 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀሙ ላይ ከማኔጅመንት አባላት፣ ዳይሬክተሮች እና ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት በዓድዋ መታሠቢያ ያካሄደውን የሁለት ቀናት ስብሰባ ዛሬ አጠናቅቋል።




ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!