ዓባይ ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የኢፍጣር መርሃ ግብር አከናወነ Solomon Aynishet March 22, 2025

ዓባይ ባንክ የ1446ኛውን የታላቁን የረመዳን ወር ምክንያት በማድረግ በአዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ደሴ እና ቡታጅራ ከተሞች የኢፍጣር መርሃ ግብር በትናትናው ዕለት አከናውኗል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የዓባይ ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች  የተገኙ ሲሆን፣ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ባስቀመጠው ተቋማዊ መርሁ መሠረት የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ረገድ ለወገን ያለውን አጋርነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የረመዳን ወር የአብሮነት መገለጫ ወር በመሆኑ፣ ባንኩ በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የኢፍጣር መርሃግብር በማዘጋጀት ላይ ይገኛል፡፡