ዓባይ ባንክ በበጎ አድራጎት ተግባር ላበረከተው አስተዋጽዖ ከዝግባ የሕጻናትና አረጋውያን የበጎ አድራጎት ድርጅት የዕውቅና የምሥክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡
በዕለቱ የዝግባ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስለሺ ጌታቸው እንደገለጹት፣ ዓባይ ባንክ ድርጅቱን በመደገፍ እያበረከተው ላለው ግዙፍ የማኅበራዊ ኃላፊነት ከፍተኛ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀጣይም ሌሎች ተቋማት በዘላቂነት ድርጅቱን በመደገፍ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ዓባይ ባንክ የ15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር የመዝጊያ ሥነ-ስርዓት የማጠቃለያ መርሐ-ግብር ላይ ነው የ2,000,000 ብር ድጋፉን ለድርጅቱ ያስረከበው። ከዝግባ በተጨማሪ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት መርጃ ማዕከል እና ለነህምያ የኦቲዝም ማዕከል ለእያንዳንዳቸው የ2,000,000 ብር ድጋፍ፣ በድምሩ የ6,000,000 ብር ድጋፍ አበርክቷል። በዚሁ የ15ኛ ዓመት አከባበር ወቅት ለሜቄዶንያ አረጋውያን እና ዐዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከልም 10,000,000 ብር መደገፉ ይታወሳል።
ዓባይ ባንክ በተለይም ለሕጻናት፣ አረጋውያን እና ዐዕምሮ ሕሙማን ላይ አተኩረው ለሚሰሩ እና በማኅበረሰቡ ውስጥ አወንታዊ ለውጥ የሚያመጡ ተቋማትን በባንኩ የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት ፕሮግራሞች ትኩረት በመስጠት ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።



ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!