ዓባይ ባንክ በሰዲቅ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ልዩ የደንበኞች ንቅናቄ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዕውቅና ሰጠ Solomon Aynishet January 18, 2025

ዓባይ ባንክ በሰዲቅ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ልዩ የደንበኞች ንቅናቄ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዕውቅና ሰጠ

1

ዓባይ ባንክ ከኅዳር 06 እስከ ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም ድረስ ባካሄደው ሰዲቅ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ልዩ የደንበኞች ንቅናቄ መርሃ ግብር የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች እና ቅርንጫፎች የእውቅና ሠርተፊኬት እና የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል። በመርሃ ግብሩ በአጠቃላይ አፈፃፀም ከሁሉም ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች ድሬዳዋ ዲስትሪክት እና መገናኛ ቅርንጫፍ አንደኛ በመውጣት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በሥነ – ሥርዓቱ ላይ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽ/ቤቶች እና ቅርንጫፎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣  ባንኩ እያስመዘገበ ባለው ሁለንተናዊ ዕድገት ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሊበረታታ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በሰዲቅ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞችን የሚመጥኑ ዘርፍ ብዙ አገልግሎችን በማጎልበት ስኬታማ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ዓባይ ባንክ ለሁለት ቀናት ያካሄደው የ2024/25 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ የባንኩ ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ በሰጡት ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ተጠናቅቋል፡፡

Write a comment
Your email address will not be published.