ዓባይ ባንክ በዓመታዊው የሥራ አፈጻጸም ስብሰባ በ2024/25 በጀት ዓመት በአጠቃላይ ሥራ አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች እውቅና ሰጥቷል።
የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠ ለተሸላሚዎቹ የማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና ሠርተፊኬት ሰጥተዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዕውቅና አሰጣጥ ሥነሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባንኩ በ2024/25 በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን አስታውሰው፣ በቀጣይም መላው የባንኩ ማኅበረሰብ ባንኩ የበለጠ አመርቂ ውጤት ለማስመዘገብ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ የኋላ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቀጠና ጽሕፈት ቤቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ሐምሌ 14 እና 15 በኃይሌ ግራንድ ሆቴል የተካሄደው ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ስብሰባ አቶ የኋላ ገሠሠ ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት እና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች መመሪያ ተጠናቅቋል።