ዓባይ ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ Solomon Aynishet January 27, 2026

ዓባይ ባንክ ለዳሸን ባንክ 30ኛ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

20260126145855 0I2A0516

ዓባይ ባንክ ዳሸን ባንክ ሥራ የጀመረበትን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የባንኩ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት የመልካም ምኞት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ከዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ የኋላ ገሠሠ የተላከውን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለዳሸን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በክብር አድርሰዋል፡፡

የዓባይ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የኋላ ገሠሠን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሠፋ ተፈራ ሲሆኑ፣ ዳሸን ባንክ ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገት የራሱን ጉልህ አስተዋጽዖ እያበረከተ እዚህ ደረጃ የደረሰ ባንክ መሆኑን ገልጸው፣ ለ30ኛ ዓመት የምስረታ በዓላችሁ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በበኩላቸው፣ ዓባይ በወንዙ ዳሸንም በተራራው የሀገራችን የታላቅነትና የከፍታ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በቀጣይ በትብብር በመሥራት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ይበልጥ በስኬት ወደፊት ማራመድ እንደሚቻል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዓባይ ባንክ ላቀረበው የመልካም ምኞትና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!