ዓባይ ባንክ ለቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች የስትራቴጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ አካሄደ Solomon Aynishet October 26, 2026

ዓባይ ባንክ ለቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች የስትራቴጂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ አካሄደ

photo 2026 10 24 17 03 30

ዓባይ ባንክ ከ2026/27 እስከ 2028/29 የበጀት ዓመት እንዲተገበር የተነደፈውን አዲስ የሶስት ዓመት ስትራቴጂ ዕቅድ ላይ ለቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ አካሂዷል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፑን የባንኩ የስትራቴጂ ዋና መኮንን አቶ ወንድይፍራው ታደሰ፣ የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሰፋ ተፈራ፣ የሰው ሐብት ዋና መኮንን አቶ በለጠ ቀኔ እና የብድር ትንተና እና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ አበባው አበበ በጋራ አካሂደዋል።

የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ በተለያዩ የሥራ ደረጃዎች ለሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች በተመሳሳይ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ዓባይ – የታላቅነት ምንጭ!