ዓባይ ባንክ የ5 ዓመት ስትራቴጂ ዕቅዱን እና በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የብራንድ መለያ በተመለከተ በደሴ ዲስትሪክት ስር ለሚገኙ ሠራተኞቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ በደሴ እና መቀሌ ከተሞች አካሂዷል።
የባንኩ የስትራቴጂ ዋና መኮንን አቶ ወንድይፍራው ታደሰ፣ የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሰፋ ተፈራ፣ የስትራቴጂ እና ኢኖቬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ለገሠ እና የሀብት ማሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ማርቆስ ደመቀ የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፑን ሰጥተዋል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፑ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የባንኩ ዲስትሪክቶች የተከናወነ ሲሆን፣ በቀጣይም ተመሳሳይ ወርክሾፕ በቀሪ የባንኩ ዲስትሪክቶች ስር ለሚገኙ ሠራተኞች ለመስጠት ታቅዷል።