ዓባይ ባንክ ለሠራተኞቹ የመሪነት አቅም ማጎልበቻ ስለጠና ሰጠ Solomon Aynishet November 18, 2025

ዓባይ ባንክ ለሠራተኞቹ የመሪነት አቅም ማጎልበቻ ስለጠና ሰጠ

photo 2025 11 17 10 17 16

ዓባይ ባንክ ከሁሉም ዲስትሪክቶች ለተውጣጡ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅነት እምቅ ችሎታ ላላቸው ሠራተኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የዓባይ ባንክ የሪቴል ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ አሠፋ ተፈራ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስልጠናው የባንኩን የወደፊት መሪዎች አስፈላጊ በሆኑ የአመራርና የቴክኒክ ክህሎቶች እንዲሁም ውጤታማ የአስተዳደር ልምዶችን በሚመለከት ግንዛቤ በማስጨበጥ አቅማቸውን ያሳድጋል ብለዋል።

አቶ አሠፋ ለሰልጣኞች የዕውቅና ሠርተፊኬት ያበረከቱ ሲሆን፣ በሙሉ ትጋት እና መንፈስ ስለተከታተላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዓባይ ባንክ የሰው ሐብት ዋና መኮንን አቶ በለጠ ቀኔ በበኩላቸው፣ ክህሎት እና ችሎታ ያላቸውን ሠራተኞችን በውስጥ አቅም ማፍራት ለረጅም ጊዜ ስኬት ቁልፍ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ስልጠና የእምቅ መሪዎችን አቅም ከማጎልበት በተጨማሪ የእድገትና የላቀ ብቃት ባህልን የማጎልበት ቁርጠኝነትን ያጠናክራል ብለዋል።

photo 2025 11 17 10 17 27

ዓባይ ባንክ በሰው ሐብት ልማት ላይ ኢንቨስት በማድረግ ግለሰቦችን ለወደፊት ሚናዎች ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ባንኩ በየደረጃው ባለው ጠንካራ አመራርና ዕውቀት ማጎልበትን እያረጋገጠ መሆኑንም አቶ በለጠ ገልጸዋል።

ባንኩ በውስጥ አቅም ተመሳሳይ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት የሠራተኞችን ዕውቀትና ክህሎት ግንባታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳውቋል።

Write a comment
Your email address will not be published.